Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአማራ ክልል የወረዳ ማኅበረሰብ ተወካዮች የአጀንዳ ማሰባሰብ ምዕራፍ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የአማራ ክልል የወረዳ ማኅበረሰብ ተወካዮች የአጀንዳ ማሰባሰብ ምዕራፍ በስኬት መጠናቀቁን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ከመጋቢት 27 ቀን 2017 ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ሲያካሂድ የቆየው የመጀመሪያው ምዕራፍ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት መጠናቀቁን ኮሚሽነር መላኩ ወልደማርያም በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል፡፡

ከ263 ወረዳዎች ከተወከሉ 4 ሺህ 500 የማኅበረሰብ ወኪሎች አጀንዳ የማሰባሰብ ሥራ መከናወኑን ገልጸው፤ ሂደቱ አሳታፊና አካታች፣ ግልጽነት የተሞላበት እና በነጻነት የተካሄደ ነው ብለዋል።

በተሳታፊዎቹ ለሀገር የሚጠቅሙ ትላልቅ አጀንዳዎች መነሳታቸውንም ጠቁመዋል።

ተሳታፊዎቹ 270 የማኅበረሰብ ወኪሎችን መምረጣቸውን ጠቅሰው፤ እነዚህ ወኪሎች ነገ በሚካሄደው የባለድርሻ አካላት አጀንዳ የማሰባሰብ የምክክር መድረክ ላይ እንደሚሳተፉ አመላክተዋል፡፡

በመሳፍንት እያዩ

Exit mobile version