አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኮሪደር ልማት ሥራው የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ ሠርቶ የመኖር ባህልን እያጠናከረ መሆኑን የሐረሪ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ፡፡
ርዕሰ መሥተዳድሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት፤ “ሠርቶ ጥሮ ግሮ ለሚኖር” ያላቸውን ክብር እና አድናቆት ገልጸዋል፡፡
በክልሉ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት ሥራም የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ፤ ሠርቶ የመኖር ባህልን እያጠናከረ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡