የሀገር ውስጥ ዜና

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ለአፍሪካ ቀዳማዊ እመቤቶች ፕሬዚዳንት እና ም/ፕሬዚዳንት አቀባበል አደረጉ

By ዮሐንስ ደርበው

April 09, 2025

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለአፍሪካ ቀዳማዊ እመቤቶች ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንት የእንኳን ደህና መጣቹህ አቀባበል አደረጉ፡፡

ቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፤ የሴራሊዮን ቀዳማዊት እመቤት ፋቲማ ማዳ ባዮን (ዶ/ር) እና የአንጎላ ቀዳማዊት እመቤት አና አፎንሶ ዲያስን አዲሱን ሥራችሁን ለመረከብ እንኳን ወደ አፍሪካ መዲና አዲስ አበባ በደህና መጣችሁ ብለዋል።