የሀገር ውስጥ ዜና

በኦሮሚያ ክልል የሆቴሎች ዳግም ኮከብ ምዘና ሥራ ተጀመረ

By Melaku Gedif

April 10, 2025

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቱሪዝም ሚኒስቴር በኦሮሚያ ክልል ለሚገኙ ሆቴሎች ዳግም የደረጃ ምዘና ሥራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር አካሂዷል፡፡

በሚኒስቴሩ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ብቃት ማረጋገጥና ደረጃ ምደባ መሪ ስራ አስፈፃሚ ታሪኩ ደምሴ÷ በክልሉ የዳግም ደረጃ ምደባ ሥራው ከ2007 ዓ.ም በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚከናወን መሆኑን አንስተዋል፡፡

የምዘና ሒደቱ በተቀመጠው አሰራር መሰረት ግልጽና ታአማኒነትን ባረጋገጠ መልኩ እንደሚከናወን ነው የተናገሩት፡፡

በሒደቱ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትና የሞያ ማህበራት በታዛቢነት እንደሚሳተፉ መጠቆማቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ምትኬ ቢሆንልኝ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷የዳግም ደረጃ ምዘና ሥራው ሆቴሎች የሚሰጡትን አገልግሎት ለማሻሻል እንደሚያግዝ ጠቅሰዋል፡፡