አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሴቶች፣ ወጣቶችና ተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎች በሀገር ሰላም ግንባታ ያላቸውን ሚና የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሰራ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር) ገለጹ።
“ሰላምን ተለማመዱ በሰላም ኑሩ” የተሰኘ ፕሮጀክት ይፋ ሆኗል።
ኤርጎጌ ተስፋዬ(ዶ/ር) በዚህ ወቅ እንዳሉት÷ ሚኒስቴሩ ሴቶች፣ ወጣቶችና ተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎች በሰላም ግንባታ ሒደት ላይ እንዲሳተፉ እየሰራ ነው።
ሰላምን በመገንባት ሥራ የአመራር ሚና እንዲኖራቸው ትኩረት መደረጉን ጠቁመው÷ማህበራዊ ትስስርን ማጠናከር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው ብለዋል፡፡
ፕሮጀክቱ ህጻናት፣ ሴቶች፡ ወጣቶች እና ተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎችን ያካተተ ጠንካራ ሀገራዊ ሰላምን ለመገንባት ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥር አስገንዝበዋል፡፡
በኤስኦሴስ የህጻናት መንደር፣ ጀርመን የዓለም ስነ ህዝብ ፋውንዴሽንና ፒ ኤች ኢ ኢትዮጵያ ጥምረት በአፋር፣ ኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች የሚተገበረው ፕሮጀክቱ ለሶስት ዓመታት የሚቆይ ነው ተብሏል።
የአውሮፓ ህብረት የፕሮጀክቱን ወጪ እንደሚሸፍን የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።