Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር በይፋ ሥራ ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ በይፋ ሥራቸውን ጀምረዋል፡፡

የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ ስብሰባ በዛሬው ዕለት የተካሄደ ሲሆን÷ ሌ/ጀነራል ታደሰ በቀጣይ ወራት በሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

በቀጣይ የክልሉን ሰላምና ደህንነት አስተማማኝ ለማድረግ የሚያስችሉ ስራዎች እንደሚከናወኑም ተገልጿል፡፡

Exit mobile version