የሀገር ውስጥ ዜና

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የ3 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አደረገ

By Melaku Gedif

April 11, 2025

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵ የ3 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

ድጋፉ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓቱን ለማጠናከር እና ተደራሽነቱን ለማስፋት የሚውል ነው ተብሏል፡፡

የተደረገው ድጋፍ የሲቪል ማህበረሰበ ድርጅቶችና በዩኒቨርሲቲዎች የሕግ ድጋፍ የሚሰጡ ማዕከላት በዘርፉ የሚያከናወኑትን ሥራ እንደሚያጠናክር የህብረቱ መረጃ ያመላክታል፡፡