አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከታንዛኒያ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሐሰን (ዶ/ር) የተላከን መልዕክት ተቀበሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ፤ ዛሬ ጠዋት ከፕሬዚደንቷ የተላከውን መልዕክት መቀበላቸውን ገልጸዋል።
መልዕክቱን ያደረሱት የታንዛኒያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት እና የአሁኗ ፕሬዚዳንት ሳሚያ ሱሉሁ ሐሰን (ዶ/ር) ልዩ መልዕክተኛ ጃካያ ሚሪሾ ኪክዌቴ (ዶ/ር) መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።