Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አቶ ደስታ ሌዳሞ የሐዋሳ ከተማ ተወዳዳሪነት ተጠናክሮ መቀጠሉን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በከፍተኛ የኢንቨስትመንት እንቅስቀሴ ውስጥ የምትገኘው ሐዋሳ ከተማ ተወዳዳሪነት ተጠናክሮ ቀጥሏል ሲሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ደስታ ሌዳሞ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሩ በሐዋሳ ከተማ እየተገነቡ ያሉ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።

አቶ ደስታ በዚሁ ወቅት ሐዋሳ ከተማ በከፍተኛ የኢንቨስትመንት እንቅስቀሴ ውስጥ መሆኗን ጠቅሰው፤ ተወዳዳሪነቷም ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል፡፡

የጉብኝቱ ዓላማ በጥሩ እንቅስቃሴ ላይ የሚገኙትን ማበረታታት፣ ወደ ኋላ የቀሩት ተጠናክረው ወደ ሥራ እንዲገቡ ለማድረግ እና እስከአሁን ወደ ሥራ ባልገቡና በማያለሙት ላይ እርምጃ ለመውሰድ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

Exit mobile version