አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ዛሬ ተጀምሯል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷በግምገማው የሚቀጥሉትን 3 ወራት ሥራዎቻችንን እቅድ ለማጠናከር የሚረዱ ውይይቶችን እናካሂዳለን ብለዋል።
እስካሁን ያሳካነው የሥራ ውጤት ሰፊ ቢሆንም ስኬታችን ሳያዘናጋን ለበለጠ ከፍታ የሚያነሳሳን ሊሆን ይገባል ነው ያሉት፡፡