አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ ቀዳማዊ እመቤቶች ፕሬዚዳንትና የሴራሊዮን ቀዳማዊት እመቤት ፋቲማ ማዳ ባዮ (ዶ/ር) እና የአፍሪካ ቀዳማዊ እመቤቶች ም/ፕሬዚዳንትና የአንጎላ ቀዳማዊት እመቤት ኣና አፎንሳ ዲያስ የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝታቸው ወቅት የዓድዋ ድል መታሰቢያ ዋና ዳይሬክተር አቶ ግሩም ግርማ አቀባበል ያደረጉላቸው መሆኑን የዓደዋ ድል መታሰቢያ መረጃ ያመላክታል፡፡