የሀገር ውስጥ ዜና

የአልጄሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ

By Mikias Ayele

April 12, 2025

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአልጄሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍ በ5ኛው የኢትዮጵያ እና አልጄሪያ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ ሀደራ አበራ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

5ኛው የኢትዮ-አልጄሪያ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ነገ የሚጀመር ሲሆን÷በዛሬው ዕለት የሁለቱ ሀገራት የጋራ ኮሚሽን የቴክኒክ ስብሰባ መካሄድ ጀምሯል፡፡