Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የብልጽግና ግባችንን ለማሳካት ተቋማት ቀን ከሌት ሊተጉ ይገባል – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሀገራዊ የብልጽግና ግባችንን እና ዓመታዊ እቅዶቻችንን ለማሳካት ተቋማት ቀን ከሌት ሊተጉ ይገባል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አሳሰቡ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የ2017 በጀት ዓመት የ9 ወራት ዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚና የዘርፎች ዕቅድ አፈጻጸም ከፌደራል ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ጋር መገምገም መጀመሩን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

በግምገማው በ100 ቀናት የትኩረት ማዕከል የሆኑ ዋና ዋና ተግባራት፣ የተገኙ ውጤቶችን፣ የታዩ ክፍተቶችንና የትኩረት አቅጣጫዎች ከተቋማቱ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በጋራ እናያለን ብለዋል፡፡

ባለፉት 9 ወራት በተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚና ሪፎርም ትግበራ በተለያዩ መስኮች በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል ነው ያሉት፡፡

የዘርፎች አፈጻጸምም የላቀ ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን÷እነዚህ ድሎቻችን እንደ መንግስት የመፈፀም አቅማችንን ማሳያዎች ናቸው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም በቀሪ ወራት መፈፀም ያለባቸውን ተግባራት በመለየት በዓመቱ ለማሳካት የተያዙ ትልሞችን በተሟላ መልኩ ለመፈፀም ሁሉም አካላት በትኩረት እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡

Exit mobile version