Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በትግራይ ክልል 2ኛው ዙር የሴፍቲኔት ፕሮግራም ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በትግራይ ክልል በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ 2ኛው ዙር የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ዛሬ በመቐለ ከተማ ተጀምሯል።

የፌዴራል መንግስት በመደበው ከ670 ሚሊየን ብር በላይ በጀት ወደ ተግባር የገባው ፕሮግራሙ ከ3 ሺህ 447 በላይ የቤተሰብ መሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

የመቐለ ከተማ የሴፍቲኔት ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ተሻለ ብርሃነ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎች እያዳንዳቸው ቢያንስ አራት ቤተሰቦችን የሚያስተዳድሩ ናቸው።

የ2ኛው ዙር የሴፍቲኔት ፕሮግራም ተጠቃሚዎችን ለ3 ዓመታት በተለያዩ ሥራዎች ላይ በማሳተፍ ዘላቂ የገቢ ምንጭ ወደሚያገኙበት የሥራ ሁኔታ እንዲሸጋገሩ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።

በመጀመሪያው ዙር የሴፍትኔት ፕሮግራም ተጠቃሚ የነበሩ 3 ሺህ 215 የቤተሰብ መሪዎች በቀጣዩ ወር እንደሚመረቁ መግለጻቸውንም ኢዜአ ዘግቧል።

Exit mobile version