አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ከጅቡቲ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱልቃድር ካሚል ሞሀመድ ጋር ተወያይተዋል፡፡
አምባሳደር ብርሃኑ በጅቡቲ በነበራቸው የስራ ቆይታ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የኢትዮ-ጅቡቲ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ እንዲጠናከር ላበረከቱት ወንድማዊ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የረጅም ዓመታት ወዳጅነት በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን ዕምነት መግለፃቸውን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኢምባሲ መረጃ አመላክቷል።