ስፓርት

5ኛው ስፖርት ለልማትና ለሠላም ቀን እየተከበረ ነው

By Yonas Getnet

April 14, 2025

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 5ኛው ሀገር አቀፍ ስፖርት ለልማት እና ለሠላም ቀን በኦሮሚያ ክልል ደምቢዶሎ ከተማ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከኦሮሚያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር የሚከበረው ቀኑ፤ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና በፓናል ውይይት እየተከበረ መሆኑ ተገልጿል።

በፓናል ውይይቱ ላይ ስፖርት ለሠላምና ለልማት ጉልህ አበርክቶ ያለው በመሆኑ ለሁለንተናዊ ሀገራዊ ብልፅግና መጠቀም እንደሚገባ ተመላክቷል።

በተጨማሪም የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ባህሉ ያደረገ ማህበረሰብ በመገንባትም ጤናማ፣ ብቁ እና ተወዳዳሪ ዜጋን መፍጠር ይገባል ተብሏል ።

በመድረኩ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ መኪዩ መሐመድ፣ የኦሮሚያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ም/ኃላፊ ደሣለኝ ጥላሁን፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጂራን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል።

5ኛው ሀገር አቀፍ ስፖርት ለልማት እና ለሠላም ቀን አከባበር በነገው ዕለት የሚቀጥል ሲሆን የደምቢዶሎ ከተማ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን ያሳተፈ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ይከናወናል።