አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የማዕድን ሚኒስትር ሃብታሙ ተገኘ (ኢ/ር) ከቤላሩስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማክሲም ሪዤንኮፍ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በማዕድን እና በተለያዩ ዘርፎች ላይ በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ለይ መክረዋል፡፡
በተለይም በማዕድን ፍለጋና ልማት ቴክኖሎጂ እንዲሁም በሰው ሃብት ልማት በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
ማክሲም ሪዤንኮፍ÷ቤላሩስ ለኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ ያላትን ልምድ ለማካፈልና የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር እንደምትፈልግ ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም የጋራ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በተለያዩ መስኮች ላይ በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል፡፡