የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያና ቤላሩስ ወታደራዊ ትብብራቸውን ለማጠናከር መከሩ

By Mikias Ayele

April 14, 2025

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሃመድ (ኢ/ር) ከቤላሩስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማክሲም ሪዚሄንኮቭ ጋር ተወያይተዋል፡፡፡

በውይይታቸውም ሀገራቱ በወታደራዊ እና ጸጥታ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ማስፋትና ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

አይሻ መሃመድ (ኢ/ር) በዚሁ ወቅት÷ ሁለቱ ሀገራት የጋራ እሴት፣ ታሪክና የባህል መመሳሰል ያላቸው መሆኑን አውስተዋል፡፡

ይህንን እንደ መልካም አጋጣሚ በመውሰድ የሁለትዮሽ ትብብሩን ይበልጥ ለማሳደግ ኢትዮጵያ ፍላጎት እንዳላት ተናግረዋል፡፡

ማክሲም ሪዚሄንኮቭ በበኩላቸው÷ ሁለቱ ሀገራት በወታደራዊ ስልጠና፣ በመከላከያ ቴክኖሎጂ ልውውጥና በመሳሰሉ መስኮች ያላቸውን ትብብር ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የሀገራቱን ሁለንተናዊ ትብብር  ይበልጥ ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውንም የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡