የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቬይትናም ይፋዊ ጉብኝት ላይ ናቸው

By Adimasu Aragawu

April 15, 2025

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በቬይትናም ሀኖይ ይፋዊ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ2025 የፒ4ጂ ቬይትናም ጉባኤ ላይም ይሳተፋሉ።

በቆይታቸው ከቬይትናም የፀሃይ ኃይል ማመንጫዎች በማምረት ወደ ውጭ የሚልከውን ቶዮ ሶላር የተባለውን ፋብሪካ ጎብኝተዋል።

ድርጅቱ በቅርቡ በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ በመግባት በኢትዮጵያ ሥራ ጀምሯል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድርጅቱ ከፀሃይ ኃይል ማመንጫ ምርት ባሻገር የኃይል ማመንጫ ፋብሪካ እንዲያቋቁም አበረታተዋል።

ይህም ኢትዮጵያ ከያዘችው የአረንጓዴ አሻራ ፖሊሲ ጋር የተናበበ በማደግ ላይ ላለው የኃይል ጥያቄ ምላሽ በመስጠት ሊያግዝ የሚችል መሆኑን መግለጻቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል።