ስፓርት

የ5ኛው ስፖርት ለልማትና ለሠላም ቀን ማጠቃለያ መርሐ-ግብር ተካሄደ

By ዮሐንስ ደርበው

April 15, 2025

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ5ኛው ሀገር አቀፍ ስፖርት ለልማት እና ለሠላም ቀን በኦሮሚያ ክልል ደምቢዶሎ ከተማ በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከኦሮሚያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ይህ መርሐ-ግብር፤ የፓናል ውይይትን ጨምሮ በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል።

በሁነቶቹ ስፖርት ለሠላምና ለልማት ጉልህ አበርክቶ ያለው በመሆኑ፤ ለሁለንተናዊ ሀገራዊ ብልፅግና መጠቀም እንደሚገባ ተመላክቷል።

በተጨማሪም የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ባህሉ ያደረገ ማህበረሰብ በመገንባት፤ ጤናማ፣ ብቁ እና ተወዳዳሪ ዜጋን መፍጠር ይገባል ተብሏል።

5ኛው ሀገር አቀፍ ስፖርት ለልማት እና ለሠላም ቀን አከባበር ዛሬ የተጠናቀቀ ሲሆን፤ በማጠቃለያ መርሐ-ግብሩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተደርጓል።