Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኢትዮጵያ እና ቬትናም በተለያዩ መስኮች በትብብር ለመሥራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና ቬትናም በንግድ እና በትምህርት ዘርፎች በትብብር ለመሥራት የሚያስችሏቸውን የመግባቢያ ስምምነቶች ተፈራረሙ፡፡

የቬትናም ጠቅላይ ሚኒስትር ፋም ሚን ቺን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቤተ-መንግሥታቸው ይፋዊ የአቀባበል ሥነ-ሥርዓት አድርገውላቸዋል።

ከአቀባበል ሥነ-ሥርዓቱ በኋላ ሁለቱ መሪዎችና የልዑካን ቡድኖቻቸው የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።

በውይይታቸውም፤ በሁለቱ ሀገራት የተካሄዱ ማሻሻያዎችን፣ ለትብበር የሚሆኑ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን በተለይም የልምድ ልውውጥንና ኢንቨስትመንትን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሐሳብ ተለዋውጠዋል።

እንዲሁም የሀገራቱ መሪዎች በንግድ እና በትምህርት ትብብር ላይ የመግባቢያ ስምምነቶች መፈራረማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

በተጨማሪም በአዲስ አበባ እና በሃኖይ መካከል በኢትዮጵያ አየር መንገድ የቀጥታ በረራ መንገድ የሚያመቻች የሲቪል አቪዬሽን ስምምነት ተደርጓል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የቬትናም ጉብኝት፤ በሀገራቱ መካከል ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከተመሠረተ ከ50 ዓመታት በኋላ በመንግሥት መሪ ደረጃ የመጀመሪያ ይፋዊ ጉብኝት መሆኑ ተገልጿል፡፡

Exit mobile version