አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ25ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ፋሲል ከነማን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የኢትዮጵያ ቡናን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ኮንኮኒ ሀፊዝ በመጀመሪያው አጋማሽ ከመረብ አሳርፏል፡፡
ኢትዮጵያ ቡና ወደ ድል ሲመለስ ፋሲል ከነማ ከሦስት ተከታታይ ጨዋታ ድል በኋላ ሽንፈት አስተናግዷል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ቡና በ39 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፤ ፋሲል ከነማ በ33 ነጥብ 8ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
የሊጉ ጨዋታ ሲቀጥል ምሽት 12 ሠዓት ላይ መቻል ከአርባ ምንጭ ከተማ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡