የሀገር ውስጥ ዜና

በክልሎች ያለው የአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም ማደጉ ተገለጸ

By Mikias Ayele

April 16, 2025

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት ዘጠኝ ወራት በክልሎች መካከል ያለው የአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም ከፍ ማለቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ገለጹ፡፡

የሚኒስቴሩን የ2017 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም አስመልክቶ ከተቋሙ አመራሮች እና ባለሙያዎች ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡

በዚሁ ወቅት አቶ መላኩ አለበል እንዳሉት፤ በክልሎች መካከል ያለው የአምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም ከፍ ብሏል፡፡

ስኬቱ ሊመዘገብ የቻለውም፤ አዳዲስ ኢንዱስትሪዎችን ወደ ሥራ ከማስገባት አኳያ ከፍተኛ ውጤታማ ስራ በመሰራቱ ነው ብለዋል፡፡

ገቢ ምርቶችን በሀገር በቀል ምርቶች በመተካት ረገድም ከ3 ቢሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ብክነት ማዳን ተችሏል ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡