አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሃኖይ እየተገነባ የሚገኘውን ትልቅ የዘመነ ከተማ (የስማርት ሲቲ) ፕሮጀክት ጎብኝተዋል።
ይህም ለኢትዮጵያ የከተማ ልማት ሥራ የሚሆን ተሞክሮ የመቅሰም ተግባር አካል መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ አስታውቋል፡፡
ጉብኝቱ ዓለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር በኢትዮጵያ እየተካሄዱ ያሉ የዘመናዊ ከተማ ፕሮጀክቶችን ለማላቅ የሚደረግ ፍላጎትና ጥረትን ያሳያል ተብሏል።