የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ በትንሳኤ በዓል የምርት አቅርቦት አስተማማኝ እንዲሆን ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ

By Mikias Ayele

April 16, 2025

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለትንሳኤ በዓል አስፈላጊ የሆኑ ምርቶች አቅርቦት አስተማማኝ እንዲሆን ዝግጅት መደረጉን የአስተዳደሩ ንግድ ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ሀላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ በሰጡት መግለጫ÷ ማህበረሰቡ ያለምንም የአቅርቦት ችግር በዓሉን እንዲያሳልፍ ቀደም ብሎ ዕቅድ በማውጣት ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን ተናግረዋል።

መንግስት ያስገነባቸውን የገበያ ማዕከላት ጨምሮ በአዲስ አበባ የንግድ ድርጅቶች፣ በህብረት ስራ ማህበራት፣ በቅዳሜና እሁድ ገበያዎች እንዲሁም በሌሎች አማራጮች ምርቶቹን ተደራሽ ለማድረግ ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰዋል።

በዚህም አሁን ላይ ሁሉንም አማራጮች በመጠቀም የምርት አቅርቦት ለህብረተሰቡ በስፋት እየደረሰ መሆኑን ገልጸው፤ ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖር የቁጥጥር ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡

በጀማል አህመድ