Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኢትዮጵያ ኮሪያ ዘማቾችን ገድል ለትውልድ ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ ሐውልት፣ ሙዚየምእንዲሁም አዳራሽ የእድሳት ሥራ ተጠናቅቆ ዛሬ ተመርቋል።

በዚሁ ወቅትም የኢትዮጵያ ኮሪያ ዘማቾች አኩሪ ገድል ክብሩ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ የዘማቾች ሐውልት ታሪኩን በሚመጥን መልኩ እድሳት እንደተደረገለት ተገልጿል፡፡

እድሳቱ የሀገራቱን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደሚያጠናክር መገለጹን የመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ መረጃ አመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ኮሪያ ዘማቾችና የዘማች ቤተሠቦች የጀግኖች ዓርበኞችን ታሪክ የሚገልፅ የአልባሳት ስጦታ እንደተበረከተላቸውም ተጠቅሷል፡፡

Exit mobile version