አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሰላም ሚኒስቴር የበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡
የሰላም ሚኒስትር መሀመድ እድሪስ፤ ተቋማዊ የሪፎርምና የማስፈፀም አቅምን ከማሳደግ፣ ዘላቂ ሰላም ከመገንባት፣ ገዥ ትርክትን ከማስረፅ፣ ግጭትን አስቀድሞ ከመከላከልና ከመፍታት፣ የፌዴራል ስርዓቱን እና የመንግስታት ግንኙነትን ከማጠናከር አንፃር የተገኙ ውጤቶችን አብራርተዋል፡፡የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ
ፍቃዱ ተሰማ በበኩላቸው፤ በማክሮ ኢኮኖሚ ላይ እየተሠሩ ያሉ ሥራዎች መጠናከር ለበርካታ ችግሮች መፍትሔ እንደሚሆኑ አስገንዝበዋል፡፡
የብሔረ መንግሥት ግንባታ አለመጠናቀቅ፤ የሀገራችን ትልቁ ችግር ነው ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡
ሚኒስቴሩ ገዥ ትርክት ላይ ትኩረት አድርጎ የሰዎችን አስተሳሰብ በበጎ መልኩ ለመገንበት የየጀመራቸውን ተግባራት አጠናክሮ እንዲቀጥልም አሳስበዋል፡፡
ሀገራዊ አንድነትን ሊሸረሽሩ የሚችሉ የግጭት መንኤዎችን በመለየት በጥብቅ ዲስፕሊን መፍታት ላይ ትኩረት አድርጎ መሥራት እንዳለበትም አመላክተዋል፡፡
በተጨማሪም አሰባሳቢ የወል ትርክት ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ እና ሁሉም ማኅበረሰብ ብሔረ መንግስት ግንባታ ላይ እንዲሠራ ጠይቀዋል፡፡