አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጸሎተ ሐሙስ ሥነ-ሥርዓተ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ጸባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል እየተከናወነ ነው፡፡
በሥነ-ሥርዓቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን ጨምሮ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ቀሳውስትና ምዕመናን ተገኝተዋል።
የእምነቱ ተከታዮች ኢየሱስ ክርስቶስ ዝቅ ብሎ ለሓዋርያቱ ያሳየውን ትሕትና በሕይወታቸው ሊገልጡት እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡
ጸሎተ ሀሙስ ኢየሱስ ክርስቶስ ዝቅ ብሎ የሓዋርያቱን እግር ያጠበበት እና ትሕትናን ያስተማረበት ዕለት ነው።
በቅድስት አባተ