አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ ከተባበሩት መንግስታት የፕሮጀክት አገልግሎት ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ጆርጅ ሞሪኤራ ዳ ሲልቫ ጋር ተወያይተዋል፡፡
የጽሕፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ ተቋማቸው የኢትዮጵያን የእድገት አጀንዳዎች መደገፍ የሚችልበት አግባብ ላይ ከገንዘብ ሚኒስትሩ ጋር መወያየታቸውን ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም የትግራይ ክልልን መልሶ መገንባት ላይ እንዲሁም ዘላቂ እድገትን በመደገፍ ረገድ ሁለቱ ወገኖች በጋራ ለመስራት እና ግንኙነታቸውን ለማጠናከር መስማማታቸውን ጠቁመዋል፡፡