አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች እየታሰበ ይገኛል፡፡
በሥነ-ሥርዓቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን ጨምሮ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ቀሳውስት እና የእምነቱ ተከታዮች ተገኝተዋል፡፡
ዕለቱ በጾም፣ በጸሎት፣ በስግደት እና በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ነው እየታሰበ የሚገኘው፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ አርብ ለሰው ልጆች ሲል የከፈለውን ሕመምና ስቃይ የሚያወሱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም እየተነበቡ ይገኛሉ፡፡
በዙፋን ካሳሁን