አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል ቸርነት እና ፍቅርን ዘወትር እናደርግ ዘንድ የሚያስታውሰን ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ እየሱስ ፕሬዚዳንት ቄስ ዮናስ ይገዙ (ዶ/ር) ገለጹ።
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ እየሱስ አማኞች የስቅለት በዓልን በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች አስበዋል።
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ እየሱስ ፕሬዚዳንት ቄስ ዮናስ ይገዙ (ዶ/ር) እንደገለጹት፥ በዓሉ እግዚአብሄር ለሰው ልጆች ፍቅርን እና መስዋእትነትን ያሳየበት ነው።
በመሆኑም የእምነቱ ተከታዮች በዓሉን ሲያከብሩ የይቅር ባይነትን መንፈስ በመላበስ በአብሮነት መሆን እንዳለበት አስገንዝበዋል።
በዓሉ ቸርነትን እርስ በርስ እናደርግ ዘንድ የሚያስታውሰን መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
ቸርነትን የምናደርገው በዓልን ጠብቀን ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜ በችግር ላሉ ኑሮ ለጎደለባቸው ህይወት ለከበደባቸው ዘውትር እያደረግን መሆን እንዳለበትም ተናግረዋል።
የስቅለት በዓል ክርስቶስ ለሰው ልጆች ፍጹም ፍቅርን ያሳየበት ሲሆን÷በዓሉ የፍቅር መገለጫ መሆኑን እና ሁሉም እርስ በርሱ እንዲዋደድ ትምህርት እንደሚሰጥ ተመላክቷል፡፡
በግዛቸው ግርማዬ