የሀገር ውስጥ ዜና

 በበዓል ወቅት በዲጂታል ክፍያ ስንፈጽም ልንተገብራቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች፡-

By Mikias Ayele

April 18, 2025

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በበዓላት ወቅት ሸማቾች በዲጂታል ምህዳሩ ውስጥ ግብይቶችን ሲፈጽሙ ለከፍተኛ መጭበርበር ሊጋለጡ ይችላሉ።

ምክንያቱም አጭበርባሪዎች ይህ ወቅት ከፍተኛ ግብይት የሚፈጸምበትና ሸማቾች ሃሳባቸው በበዓል ጉዳዮች እንደሚጠመድ ስለሚያውቁ የተለያዩ የማጭበርበሪያ ስልቶችን በመጠቀም ጥቃት ስለሚያደርሱ ነው።

በመሆኑም በበዓል ሸመታ ወቅት ለአጭበርባሪዎች እንዳንጋለጥ ልንተገብራቸው የሚገቡ ጉዳዮች

እንደሚከተለው ቀርበዋል፦

👉ምርትና አገልግሎቶችን በዲጂታል አማራጮች ስንገዛ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ፤

👉የተላከልዎትን መልዕክቶች ከመክፈትዎ በፊት ትክክለኛነቱን ማረጋገጥ፤

👉የሚጠቀሙበት ስልክ ወይም ላፕቶፕ አፕሊኬሽኖችን ማዘመን፤

👉ጠንካራ የይለፍ ቃላትን መጠቀም፤

👉ባለብዙ ደረጃ የደህንነት ማረጋገጫን መተግበር፤

👉ደህንነቱ የተጠበቀ የክፍያ ዘዴዎችን መጠቀም፤

👉የግል ወይም የፋይናንስ መረጃ ከማስገባታችን በፊት የድረ-ገጹን የፕራይቬሲ ፖሊሲዎች መፈተሽ፤

#የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር