ስፓርት

ሀድያ ሆሳዕና ወላይታ ድቻን አሸነፈ

By ዮሐንስ ደርበው

April 19, 2025

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ26ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሀድያ ሆሳዕና ወላይታ ድቻን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የሀድያ ሆሳዕናን የማሸነፊያ ግቦች ብሩክ በየነ፣ በየነ ባንጃ እና ደስታ ዋሚሾ ሲያስቆጥሩ፤ የወላይታ ድቻን ብቸኛ ጎል ዘላለም አባተ ከመረብ አሳርፏል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም ሀድያ ሆሳዕና ወደ ድል ሲመለስ፤ ወላይታ ድቻ ተከታታይ ሁለተኛ ሽንፈት አስተናግዷል፡፡

በዚህም ሀድያ ሆሳዕና በ37 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፤ ወላይታ ድቻ በተመሳሳይ 37 ነጥብ በመሰብሰብ በግብ ክፍያ ተበልጦ 5ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

የሊጉ ጨዋታ ሲቀጥል ምሽት 12 ሠዓት ላይ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡