Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ቅዱስ ጊዮርጊስ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ26ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስን የማሸነፊያ ግቦች፤ ቢንያም ፍቅሩ (2) እና አብዱ ሳሚዮ ሲያስቆጥሩ፤ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን ከሽንፈት ያልታደገች ብቸኛ ግብ ደግሞ ቡልቻ ሹራ ከመረብ አሳርፏል፡፡

ፈረሰኞቹ ከሁለት ተከታታይ ሽንፈት በኋላ ወደ ድል የተመለሱበትን ውጤት አስመዝግበዋል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ34 ነጥብ 9ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፤ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በ11 ነጥብ ወራጅ ቀጠና 18ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

Exit mobile version