አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የትንሣኤ በዓልን በማስመልከት በጾም በጸሎት ያሳለፉ ድጋፍ የሚሹ ወገኖች፣ አካል ጉዳተኞች እና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች የተጋለጡ ወገኖችን አስፈስከዋል።
ፆም የምናስፈታው በባህላችን መሰረት ሌሎች ፆም በሌሊት ሲፈቱ እና በዓሉን በድምቀት ሲያከብሩ ጠያቂ የሌላቸው አረጋውያን፣ የሀገር ባለውለታዎች እና ለተለያዩ ማህበራዊ ችግር የተጋለጡ ወገኖች የጾሙን ወቅት በጾም እና በጸሎት አሳልፈው በፍቺው ጊዜ ባይተዋርነት እንዳይሰማቸው ሁሌም ከተማቸው እንደማይዘነጋቸው ለማሳየት እና ፍቅር ለመግለፅ እንደሆነ ነው ብለዋል።
በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር እና የደስታ እንዲሆንላቸውም መልካም ምኞታቸውን መግለጻቸውን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል።