Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የትንሣኤ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የትንሣኤ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉን በማስመልከት የሃይማኖት አባቶች ባስተላለፉት መልዕክት በዓለ ትንሣኤ የእግዚአብሔር ፍቅር መገለጫና የተስፋችን ማሳያ መሆኑን ልንገነዘብ ይገባል ብለዋል።

በዓለ ትንሣኤውን ስናከብርም ለእግዚአብሄር ክብርና ለሰው ልጆች ደኀንነት በአንድነት በመቆም መሆን እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

የትንሣኤ በዓል የክርስቶስን መነሣት ያስተማረን የምሥራች መሆኑንም ተናግረዋል።

የትንሣኤ በዓል ሲከበር የችግሮች ሁሉ መውጫ ቁልፍ ሰላም ብቻ በመሆኑ በትንሣኤው ብርሃን ለሀገርና ለህዝብ የሰላም መሣሪያ በመሆንና ለሰላም በመፀለይ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

ምዕመኑ የትንሣኤን በዓል ሲያከብር ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ወገኖች በማገዝ ሊሆን ይገባልም ነው ያሉት።

በክርስቶስ ትንሣኤ ሁሉም በፍቅር ልብና በይቅርታ ለሰላምና አብሮነት በመጸለይ በዓሉን እንዲያከበርም መልዕክት አስተላልፈዋል።

Exit mobile version