አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ 26ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ቡናን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ቀን 9 ሠዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ ሲዳማ ቡና ፍቅረየሱስ ተክለብርሃን ባስቆጠራት ብቸኛ ግብ ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥቷል።
የሊጉ ጨዋታ አመሻሽ 12 ሠዓት ላይ ቀጥሎ ሲካሄድ አርባ ምንጭ ከተማ እና ስሑል ሽረ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡