ስፓርት

አርሰናል ሲያሸነፍ ማንቼስተር ዩናይትድ ተሸነፈ

By Mikias Ayele

April 20, 2025

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 33ኛ ሳምንት መርሐ ግብር አርሰናል ከሜዳው ውጪ ኢፕስዊች ታውንን ሲያሸንፍ ማንቼስተር ዩናይትድ ሽንፈት አስተናግዷል፡፡

ቀን 10 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ አርሰናል ኢፕስዊች ታውንን 4 ለ 0 አሸንፏል፡፡

አርሰናል የጨዋታ ብልጫ በወሰደበት ጨዋታ ሊያንድሮ ትሮሳርድ (2)፣ ጋብርኤል ማርቲኔሊ እና ኢታን ኒዋኔሪ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

በተመሳሳይ በተደረገ ሌላ ጨዋታ ማንቼስተር ዩናይትድ በሜዳው ፓብሎ ሳራቢያ ባስቆጠራት ግብ በወልቭስ 1 ለ 0 ተሸንፏል፡፡

ሽንፈቱ ማንቼስተር በውድድር ዘመኑ ያስተናገደው 15ኛ ጨዋታ ሆኖ ተመዝግቧል።

በተመሳሳይ ሰዓት በተደረገው የቼልሲ እና ፉልሃም ጨዋታ ድራማዊ ትዕይንትን አስተናግዶ በቼልሲ 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

በጨዋታው ፉልሃም በአሌክስ ኢዮቢ ግብ እስከ 84ኛው ደቂቃ ሲመራ ቢቆይም ታዳጊው ትሬቅ ጆርጅ በ85 እንዲሁም ፔድሮ ኔቶ በጭማሪ ደቂቃ ግብ አስቆጥረው ቼልሲ አሸናፊ ሆኗል፡፡