አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት በርካታ ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያዎችን ከ146 ተጠርጣሪዎች ጋር መያዙን አስታውቋል፡፡
በዚህም መሠረት ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውርን ለመከላከል በተደረገ ኦፕሬሽን፤ 121 የጦር መሣሪያዎችን ከመኖሪያ ቤቶች፣ 8 ሺህ 989 ከፀረ-ሰላም ኃይሎች እና 36 የጦር መሣሪያዎችን በኬላዎች ላይ መያዙን ገልጿል፡፡
በተጨማሪም 6 ሺህ 351 የተለያዩ የጦር መሣሪያ ጥይቶች ከመኖሪያ ቤቶች፣ 8 ሺህ 989 ከፀረ-ሰላም ኃይሎች፣ 51 ሺህ 846 በኬላዎች ተይዘዋል መባሉን የፌደራል ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡
እንዲሁም 236 የተለያዩ የጦር መሣሪያ ካዝናዎች በመኖሪያ ቤቶች እና 148 በኬላዎች ላይ መያዛቸው ተጠቁሟል፡፡
በተመሳሳይ 1 ብሬን ከፀረ-ሰላም ኃይሎች፣ 2 ብሬን በኬላዎች የተያዘ ሲሆን፤ 31 የተለያዩ ቦምቦች ከመኖሪያ ቤቶች፣ 25 ቦምቦችን ከፀረ-ሰላም ኃይሎች፣ 122 ቦምቦችን በኬላዎች መያዙን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
32 የተለያዩ ሕገ-ወጥ ሽጉጦች ከመኖሪያ ቤቶች፣128 ሽጉጦች ከፀረ-ሰላም ኃይሎች፣ 102 በኬላዎች መያዝ መቻሉንም ጠቅሷል፡፡
1 ስናይፐር ከመኖሪያ ቤቶች እንዲሁም 1 ስናይፐር ከፀረ-ሰላም ኃይሎች በኤግዚቢትነት መያዙን እና 146 ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አስረድቷል፡፡
ሕብረተሰቡ ሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውርን ሲመለከት በዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ (EFPApp) እና በ991 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ በመስጠት የዜግነት ድርሻውን እንዲወጣ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል፡፡