የሀገር ውስጥ ዜና

የሰላም ሚኒስቴር በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ሕልፈት የተሰማውን ሃዘን ገለጸ

By Yonas Getnet

April 21, 2025

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሰላም ሚኒስቴር በሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ሕልፈተ ሕይወት የተሰማውን ሃዘን ገልጿል።

ሚኒስቴሩ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ሕልፈት ከፍተኛ ሃዘን ላይ ለሚገኙት የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አባቶች እና ምዕመናን መጽናናትን ተመኝቷል፡፡