ስፓርት

ባሕርዳር ከተማ መቐለ 70 እንደርታን አሸነፈ

By Melaku Gedif

April 21, 2025

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ26ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ባሕርዳር ከተማ መቐለ 70 እንደርታን 4 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የባሕርዳር ከተማን የማሸነፊያ ግቦች ቸርነት ጉግሳ እና አቤል ማሙሽ በተመሳሳይ ሁለት ሁለት ግቦችን ከመረብ አሳርፈዋል፡፡

መቐለ 70 እንደርታን ከሽንፈት ያልታደገችዋን ብቸኛ ግብ ደግሞ አሸናፊ ሀፍቱ አስቆጥሯል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ባሕርዳር ከተማ በ40 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ÷ መቐለ 70 እንደርታ በ28 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡