ስፓርት

ሊድስ ዩናይትድ እና በርንሌይ ወደ ፕርሚየር ሊጉ አደጉ

By Melaku Gedif

April 21, 2025

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሊድስ ዩናይትድ እና በርንሌይ ለ2025/26 የውድድር ዓመት ከሻምፒዮን ሺፕ ወደ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማደጋቸውን አረጋግጠዋል፡፡

ዛሬ በተደረገ የሻምፒዮን ሺፕ ጨዋታ በርንሌይ ሼፍልድ ዩናይትድን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ በርንሌይ ነጥቡን 94 በማድረስ ለቀጣዩ የውድድር ዓመት ወደ እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ማደጉን አረጋግጧል።

በተመሳሳይ ሊድስ ዩናይትድ ስቶክ ሲቲን በማሸነፍ ወደ እንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ያደገ ሌላኛው ቡድን መሆን ችሏል፡፡

በዚህም ከሁለት የውድድር ዓመታት የሻምፒዮን ሺፕ ቆይታ በኋላ ሊድስ ዩናይትድ በድጋሚ ወደ ፕርሚየር ሊግ ማደግ ችሏል፡፡

በቪንሰንት ኮምፓኒ እየተመሩ በ2023/24 የውድድር ዘመን ወደ ሻምፒዮን ሺፑ ወርዶ የነበረው በርንሌይ ከአንድ የውድድር ዓመት በኋላ ነው ወደ ፕሪሚየር ሊጉ የተመለሰው፡፡

በሌላ በኩል ሌስተር ሲቲ እና ሳውዛምፕተን ከእንግለዚዝ ፕሪሚየር ሊግ መውረዳቸውን ያረጋገጡ ክለቦች መሆናቸው ይታወሳል፡፡