Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአማራ ክልል የሌማት ትሩፋት እሳቤ ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል የሌማት ትሩፋት እሳቤ ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ መሆኑን የክልሉ እንስሣት እና ዓሣ ሀብት ልማት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ጋሻው ሙጨ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

ለአብነትም ባለፉት ዘጠኝ ወራት በክልሉ 872 ሚሊየን እንቁላል፣ ከ476 ሺህ ቶን በላይ ሥጋ፣ ከ1 ነጥብ 6 ሚሊየን ሊትር ቶን በላይ ወተት እና ከ25 ሺህ ቶን በላይ የዓሣ ምርት መገኘቱ አብራርተዋል፡፡

የሌማት ትሩፋት ሥራው የሚገኘውን ምርት በመጨመር፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ እና ከዚህ በፊት ለግብርና ሥራ የማይታሰብ የሚመስለውን የከተማ ግብርና ተግባር የተሻለ እንዲሆን በማድረግ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ጠቅሰዋል፡፡

በተለይም ማኅበራትን በማደራጀትና የገበያ ትስስር በመፍጠር ተጠቃሚነትን ከፍ ለማድረግ እንዲሁም ባለሀብቶች ምርቶችን ዕሴት ጨምረው ወደ ገበያ እንዲያቀርቡ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

በከድር መሀመድ

Exit mobile version