አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሐረሪ ክልል ከትናንት ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው የበጀት ዓመቱ የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተጠናቅቋል።
የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ በማጠቃለያው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ አመራሩ የፀና አቋም በመያዝ የተሰጠውን ኃላፊነት መወጣት እንደሚጠበቅበት አሳስበዋል፡፡
ሕዝቡን ተጠቃሚ ያደረጉ የልማት ሥራዎች በተሻለ ፍጥነትና ቅንጅት ተጠናክረው ንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል፡፡
በክልሉ ሰላምና የሕግ የበላይነት ለማረጋገጥ በላቀ ትኩረትና ቁርጠኝነት እንደሚሠራም አመላክተዋል፡፡
መንግሥታዊ አገልግሎቶችም ከመቼውም ጊዜ በላይ ፍትሐዊ፣ ጥራት ያለውና ፈጣን ሊሆኑ ይገባል ብለዋል፡፡
ሌብነት፣ ሙስናና ብልሹ አሠራርን መከላከልና ተጠያቂነትን ማስፈን ሌላው ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
በክልሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በሁሉም ዘርፎች የተከናወኑ ሥራዎች አበረታች ቢሆኑም፤ በቀጣይ በተቋማት መካከል ያለው አፈፃፀም የተመጣጠነ እንዲሆንና ያልተሳኩ ዕቅዶችን ለማሳካት ርብርብ እንዲደረግ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
በተስፋዬ ኃይሉ