አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ 4ኛ ኮርስ አዲስ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላት የተግባርና የንድፈ ሐሳብ ስልጠና በሁሉም ክፍለ ከተሞች ተጀምሯል።
ስልጠናው በአካል፣ በንድፈ ሐሳብና በተግባር የበቁ አዲስ የሰላም ሰራዊት አባላትን አሰልጥኖ ስምሪት ለመስጠት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
የቢሮው ሃላፊ ሊዲያ ግርማ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ተገኝተው ስልጠናውን ማስጀመራቸውን ከቢሮው የተገኘው መረጃ አመላክቷል።