አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባለፉት ዘጠኝ ወራት 356 ሺህ 935 አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ መሆናቸው አስታውቋል፡፡
ሰሜን አዲስ አበባ 4 ሺህ 440፣ ባሌ ሮቤ 9 ሺህ 219 እና ሆሳዕና 14 ሺህ 83 ደንበኞች አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ በማድርግ ከእቅዳቸው በላይ ያሳኩ ሪጂኖች ናቸው ተብሏል፡፡
የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ የሆኑ አዳዲስ ደንበኞች ቁጥር ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 20 በመቶ በላይ ብልጫ እንዳለው የአገልግሎቱ መረጃ ያመላክታል፡፡
በሌላ በኩል 107 አዳዲስ የገጠር ከተሞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ የተቻለ ሲሆን÷ 102 ከዋናው የኃይል ቋት 5 ደግሞ ከፀሐይ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ያገኙ መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡
ባለፉት ዘጠኝ ወራት የ15 ሺህ 295 ኪሎ ሜትር የማሳራጫ መስመር ማስፋፊያ እና 3 ሺሕ 42 አዲስ ትራንስፎርመር ተከላ ሥራ መከናወኑም ተገልጿል፡፡