የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ሙስጠፌ የታለሙ ግቦችን ለማሳካት አመራሮች በትኩረት እንዲሰሩ አሳሰቡ

By Melaku Gedif

April 24, 2025

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በመንግስት የተቀመጡ ቁልፍ ግቦችን ለማሳካት አመራሮች በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ አሳሰቡ፡፡

የሶማሌ ክልል አመራሮች በክልሉ ዞኖችና ወረዳዎች ያካሄዱት ምልከታ ሪፖርት የቀረበበት መድረክ በጅግጅጋ ከተማ ተካሂዷል።

በመድረኩ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ አመራሮች መገኘታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

አመራሮች በልማት፣ ጸጥታ፣ ፖለቲካ እና በሌሎች ጉዳዮች ከሕዝብ የተነሱ ጥያቄዎችን በውይይት መድረኩ ላይ አቅርበዋል።

ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ በዚህ ወቅት ÷ የክልሉ አመራሮች በመንግስትና በፓርቲ እቅዶች የተቀመጡ ቁልፍ ግቦችን ለማሳካት አመራሮች በትኩረት እንዲሰሩ አሳስበዋል።