የሀገር ውስጥ ዜና

በአውሶም ላይ የሚመክር ስብሰባ በዩጋንዳ እየተካሄደ ነው

By Mikias Ayele

April 25, 2025

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ ኅብረት የሶማሊያ ድጋፍና ማረጋጋት ተልዕኮ (አውሶም) ዙሪያ የሚመክር ስብሰባ በዩጋንዳ ኢንቴቤ መካሄድ ጀምሯል።

በስብሰባው ለአውሶም ሰራዊት ያዋጡ ሀገራት ተወካይ ልዑኮች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

ኢትዮጵያ በመወከል በመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሀመድ (ኢ/ር) የተመራ ልዑክ እየተሳተፈ እንደሚገኝ ከኡጋንዳ ኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡