አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የብልጽግና ፓርቲ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ከሰዓት በኋላ ጀምሮ እያካሄደ ይገኛል።
የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባወጡት ጽሁፍ፤ ከዛሬ ከሰዓት በኋላ ጀምሮ የብልጽግና ፓርቲ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በሀገራዊ ቁልፍ ጉዳዮች እንዲሁም በፓርቲ ተኮር ጭብጦች ላይ ለመጪዎቹ ሁለት ቀናት መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል ብለዋል።