የዜና ቪዲዮዎች

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ለአውሶም ሰራዊት ላዋጡ ሀገራት ምስጋና አቀረቡ

By Hailemaryam Tegegn

April 25, 2025

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ለአፍሪካ ኅብረት የሶማሊያ ድጋፍና ማረጋጋት ተልዕኮ (አውሶም) ሰራዊት ላዋጡ ሀገራት ምስጋና አቀረቡ።

በዩጋንዳ ኢንቴቤ በአውሶም ዙሪያ የመከረው ልዩ ስብሰባ ተጠናቋል።

በስብሰባው የተገኙት የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር፤ ሰራዊት በማዋጣት መስዋዕትነት እየከፈሉ ለሚገኙ ሀገራት አድናቆታቸውን በመግለጽ፤ አመስግነዋል።

ህብረቱ በሶማሊያ ሰላም ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት በቁርጠኝነት የሚደግፍ መሆኑንም አረጋግጠዋል።

በዩጋንዳ አስተናጋጅነት በተካሄደው ልዩ ስብሰባ ለአውሶም ሰራዊት ካዋጡ ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ በመከላከያ ሚኒስትር አይሻ መሀመድ (ኢ/ር) በተመራ ልዑክ አማካኝነት ተሳትፋለች።